top of page

ፓርቲዎች በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚያቀርቡት የምርጫ ማኒፌስቶ ለህዝብ ግልፅ በሆነ መልኩ እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ህብረት ጠየቀ፡፡

  • 5 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 15/2018


ፓርቲዎች በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚያቀርቡት የምርጫ ማኒፌስቶ ለህዝብ ግልፅ በሆነ መልኩ እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ህብረት ጠየቀ፡፡


የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ እስካሁን እየቀረቡ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመገናኛ ብዙሃን ክርክር ጠንካራም ደካማ ጎንም አላቸው ብሏል፡፡


የፖለቲካ ፓርቲዎች ፖሊሲያቸውን ለህዝቡ ግልጽ ማድረግ እና ባሉት አማራጮች ሁሉ ማግኘት የሚቻል አድርጎ ማስቀመጥ አለባቸውም ተብሏል፡፡

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማድረግ በጣት የሚቆጠር ወር ቢቀረውም በምርጫው ከሚወዳደሩት 47 ፓርቲዎች ክርክር የሚያደርጉትና ፖሊሲያቸውን በግልጽ የሚያስተዋወቁት ጥቂቶቹ ብቻ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ ያስረዳሉ።


መራጮች አንድን ፓርቲ የሚመርጡት አስቀድሞ ፖሊሲውን አይተውና በግልጽ መረዳት ሲችሉ ብቻ ነው ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page