ጥቅምት 8 2018 "ልዩ ባስ" የሚል መጠርያ ያለው ለሀገር አቋራጭ መንገደኞች ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ
- sheger1021fm
- 20 minutes ago
- 1 min read
አዲስ ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እና እንግዳ ትራቭል ቴክኖሎጂ በጋራ "ልዩ ባስ" የሚል መጠርያ ያለው ለሀገር አቋራጭ መንገደኞች ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂ ዛሬ ማስጀመራቸውን ተናገሩ።
ይህ ቴክኖሎጂ ደንበኞች ወይም ተጓዦች ባሉበት ቦታ ሆነው ወደየሚፈልጉበት አካባቢ ለመጓዝ "የልዩ ባስ" የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም ቲኬታቸውን በኦንላይን መቁረጥ ይችላሉ ተብሏል።
የእንግዳ ትራቭል ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ባንተአብ አብይ እንደተናገሩት ቴክኖሎጂውን ስራ ላይ ለማዋል አራት ዓመት እንደፈጀ እና አገልግሎቱን ከደንበኞች በተጨማሪ የግል ባስ ባለንብረቶች ስራቸውን ለማቀላጣፍ መጠቀም የሚችሉበት ነው ብለዋል።

ይህንን አገልግሎት ደንበኞች ቅንጡ ስልካቸውን በመጠቀም ወደቲኬት መቁረጫ ቦታ ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው መቁረጥ እንደሚችሉም ሰምተናል።
የአዲስ ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ሻኦል በበኩላቸው ይህ የክፍያ ስረዓት በትራንስፖርቱ ዘርፍ ያለውን ችግር ይቀርፋል ተብሎ እንደታመነበት አስረድተዋል።
እንግዳ ቴክኖሎጂ በ13 የኢትዮጵያ ከተማዎች ቢሮ መክፈቱን እና በ38 ቦታዎች ደንበኞች ቲኬቱን በኦንላይን ቆርጠው መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተነግሯል።
ከ19 በላይ ከሚሆኑ የግል ባሶች ወይም "ልዩ ባሶች" ጋር በጋራ እንደሚሰሩ በማስጀመሪያው መረሃግብር ላይ ሰምተናል።
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s