top of page

ጥቅምት 6 2018በየመስሪያ ቤቱ ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን በወቅቱ በማስወገድ ወይም በመጠገን ብክነትን መከላከል ያስፈልጋል ተባለ።

  • sheger1021fm
  • Oct 16
  • 1 min read

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን፤ ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮችን መልሼ በመጠገን ከ187 ሚሊየን ብር በላይ ከብክነት አድኛለሁ ብሏል።


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፈው የ2017 በጀት ዓመት 5,580 ፈርኒቸሮችንና 6,519 የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ጠግኖ ወደ አግልግሎት መመለሱን ተናግሯል።


ይህ የተነገረው ዛሬ የኤሌክትሮኒክስና የፈርኒቸር ጥገና የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው።

ree

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የንብረት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ጸሐይ መንግስቱ ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን በወቅቱ በማስወገድና በመጠገን ብክነትን መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።


ኃላፊዋ ለ2018 በጀት ዓመትም ተጠግነው አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ንብረቶች በኮሌጅ፣ በሆስፒታል፣ በጤና ጣቢያ፣ በትምህርት ቤት ወረዳ እና ክፍለ ከተማ፣ የመለየት ስራ ጨርሰናል ብለዋል።


በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ይህንኑ ሃሳብ አንስተው እንደነር ይታወሳል።


በየመንግስት ተቋማቱ ተከማችተው የሚገኙ ንብረቶችን ጠግኖ ሥራ ላይ በማዋል አለያም በመሸጥ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ይቻላል ብለው ነበር።


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - በሥራቅ አርሲ ዞን ባለንበት በጥቅምት ወር ብቻ 25 ሰዎች መገደላቸውን፣ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ተናገረ።

በኦሮሚያ ክልል በሥራቅ አርሲ ዞን ባለንበት በጥቅምት ወር ብቻ 25 ሰዎች መገደላቸውን፣ ይህንንም የተመለከተው በከባድና ጥልቅ የኃዘን ስሜት መሆኑን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ተናገረ። ቋሚ ሲኖዶስ በኦሮሚያ  ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር በጉና፣ በመርቲ፤ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page