ጥቅምት 6 2018 - ''ተገልጋዮችን የሚያንገላቱ፣ ጉቦ የሚቀበሉ ሰራተኞቼን እያባረርሁ በህግ እንዲጠየቁም እያደረግሁ ነው'' ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
- sheger1021fm
- Oct 16
- 1 min read
ተገልጋዮችን የሚያንገላቱ፣ ጉቦ የሚቀበሉ እና መሰል ጥፋቶችን የሚሰሩ ሰራተኞቼን እያባረርሁ በህግ እንዲጠየቁም እያደረግሁ ነው ሲል የከተማዋ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡
የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባና ያላገባ ሰነዶችን ማግኘትና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት ተገልጋዩን የሚያመላልሱ ሰራተኞች መኖራቸው ተነግሯል።
እነዚህን ሰራተኞች በስልጠና አግዛለው፤ አጥፍተው የሚገኙትንም መቅጣት እጀምራለሁ ብሏል ተቋሙ።
ይህንን ያሉን የኤጀንሲው ምክትል ዳሬክተር ጥጋቡ ሹመይ ናቸው።

ነዋሪዎች ከተቋሙ አገልግሎት ፈልገው በሚመጡበት ወቅት፤ ጉዳይ የሚያንዛዙ የተቋሙ ሰራተኞች እንዳሉ ደርሼበታለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡
በተለይም እንዲህ ዓይነቱ ችግር በወረዳዎች ላይ እንደሚታይ ነግረውናል፡፡
በተያያዘም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ላልሆኑ ሰዎች በሀሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የሰጡ የተቋሙ ሰራተኞችን ለህግ በማቅረብ ከስራ በማገድ እና ምንም ዓይነት ማህበራዊ አገልግሎት እንዳያገኙ መደረጉን አስረድተዋል፡፡
ችግሩን ለማስተካከል ለተቋሙ ሰራተኞች አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት መፍትሄ እየሰጠን ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx











Comments