top of page

ጥቅምት 4 2018 - ኢትዮጵያ ታሪኳን ሙሉ ከዓለም ፊት ሲያሳንሳት የቆየው አንዱና ዋና ጉዳይ የምግብ ማጣት

  • sheger1021fm
  • Oct 14
  • 1 min read

የሀገሬው ህዝብ ከገበታው ብዙ ጊዜ የሚያገኘው እንጀራ፣ ጤፍን እንኳን የጠገቡት ሀገሮች ረሃብተኞች የሚመገቡት እህል ነው የሚል ተቀጽላ እስከመስጠት የደረሱበት ነው፡፡


"አንደ ኢትዮጵያዊ፣ አንደ ሀገር ስናስበው የፖለቲካ ታሪካችን ያበላሸብን፣ ውጪ ሀገር ስንሄድ አንገታችንን የምንደፋበት፣ የምናዝንበት ጉዳይ ረሃብ በሚባለው ነው፡፡ ጤፍ ምንድነው ሲባል የረሃብተኞች ምግብ ነው ይባላል፡፡ እናንተ እኮ አልተገዛችሁም ግን ረሃብተኛ ናችሁ ይሉናል" ይላሉ የግብርና ተመራማሪው እና መምህሩ ፍሬው መክብብ(ፕ/ር)፡፡


#የምግብ ጉዳይ መልስ ለመስጠት ሀገራት አንዳላቸው አቅም መንገዳቸውም ይለያያል፡፡


ገንዘብ ካለ ምግቡ የትም ይመረት ገዝተው የሚበሉ፣ ዜጎቻቸውን የሚመግቡ ሀገራት ብዙ ናቸው፡፡


የገበሬ ሀገር ባይሆኑም ህዝባቸው የሚመገበው አያጣም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ራሳቸው አምርተው፣ ምርቱንም ተቆጣጥረው የምግብን ጥየቄ ለመመለስ የሚሰሩ አሉ፡፡ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማምጣት፡፡


ለእንደ ኢትዮጵያ ላለ ሀገር ከሌሎች ገዝቶ እንዳይበላ ብዙ የአቅም ችግር፣ አርሶም ፍጆታን ለመሸፈን ባልተቻለበት ሁኔታ የሚበጀው መንገድ በምግብ ራስን መቻል የሚለውን ብቻ መከተል ነው ወይስ በምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ መስራት?


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page