top of page

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞችን ኑሮ ለማሻሻል እና ተቀባይ ማህበረሰብን ይጠቅማል የተባለ የግብርና መስኖ ፕሮጀክት

  • 4 minutes ago
  • 1 min read

ግንቦት 14/2018


ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞችን ኑሮ ለማሻሻል እና ተቀባይ ማህበረሰብን ይጠቅማል የተባለ የግብርና መስኖ ፕሮጀክት ለማስጀመር ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ቃል ገብታ ነበር፡፡


ይሁንና ከአለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች የሚቀርበው ድጋፍ በመቀዛቀዙ ለማልማት ከታሰበው 10000 ሄክታር መሬት አሁን ላይ 1200 ሄክታር መሬት ብቻ እንደለማ ሰምተናል፡፡


በስደተኞችና ተመላሽ አገልግሎት የስደተኞች ስራ ፈጠራና የኑሮ ማሻሻያ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አንተነህ መካሻ በአለም አቀፍ የስደተኞች ፎረም ላይ ከ3 አመት በፊት መንግስት የገባውን ቃል ለመፈፀም በማሰብ 2ሺ 500 ሀኬታር መሬት በመስኖ የሚለማ አዘጋጅቶ ነበር ይላሉ፡፡



አሁን ላይ 1200 ሄክታር የሚሆነው የተዘጋጀው መሬት ብቻ ነው እስካሁን የለማው ከዚህ በላይ እንዳይሄድ አለም አቀፍ የሚቀርበው የፋይናስ አቅርቦትና ፈንድ በሚፈለገው ልክ አይደለም ብለዋል፡፡


እስካሁን ድረስም 5000 የሚሆኑ ስደተኞችና ተቀባይ ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏልም ይላሉ፡፡


ይህ የመስኖ ግብርና እየተተገበረ ያለው የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡


መንግስት ከጎረቤትና ከሌሎችም ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን ለመርዳት ፍቃደኛ ነው ነገር ግን ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚቀርበው ፈንድ እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡


ይሄ ደግሞ ስራችንን በሚፈለገው ፍጥነት እንዳንሰራ አግዶናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡


ስደተኞቹ በተጠለሉበት አካባቢ በተፈቀደላቸው ዘርፎች ብቻ እንዲሰማሩና ሀብት እንዲያፈሩ መፈቀዱንም ጠቅሰዋል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ስደተኞች ተጠልለውበት በሚገኙ መጠለያ ስፍራዎች የስደተኞች ህይወት የተሻለ ለማድረግና የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት እያደረገ ያለው ጥረት በሚፈልገው ፍጥነት እንዳያሰፋው ከአለም አቀፍ የሚመጣው ፈንድ እየቀነሰ ነው ይሄም ለስራው እንቅፋት ሆኗል ሲል የስደተኞችና ተመላሽ አገልግሎት ያስረዳል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page