top of page

ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳ ነው የተባለ ሀገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና የአፈር የማዳበሪያ ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ።

  • 6 hours ago
  • 1 min read

ግንቦት 14/2018


ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳ ነው የተባለ ሀገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና የአፈር የማዳበሪያ ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ።


ኤክስፖው አስመጭዎችን፣ አከፋፋዮችን፣ ተጠቃሚዎችን በቀጥታ የሚያገናኝ እና የገበያ ትስስርን የሚፈጥር ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል።


የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሰብል በሽታ፣ ተባይ፣ የአፈር ለምነት ችግር፣ የቴክኖሎጂ እጥረቶች እና ሌሎች ችግሮችን እያስተናገደ መሆኑ ተነግሯል።



ይህንን ችግር ለመቋቋም የሚያስችል እና ዘርፉ ያሉበትን ችግሮችን ለመፍታት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆየው ኤክስፖ የራሱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ታምኖበታል።


ዝግጅቱን ዊ ሊንክ የተባለ ድርጅት ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሌሎች የመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር እንዳሰናዳው ተነግሯል።


የሰብል በሽታ ክስተት የምርት መቀነስን እያመጣ እና ጫና እያሳደረ መሆኑ ያነሱት የዊ ሊንክ ሀላፊ እንዳለ ገብሬ (ዶ/ር) ዘርፉ ከእንዲህ አይነት ችግር እንዲወጣ ኤክስፖው ያግዛል ብለዋል።


በተጨማሪም ገበሬዎች፣ ፓሊሲ አውጭዎች፣ አስመጭዎች፣ አከፋፋዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተው ገበሬው እየገጠመው ያለውን ችግር በመለየት እና ከሌሎች የአለም ሀገራት እኩል ቴክኖሎጅን እንዲጠቀም የሚያግዝ የፓናል ውይይት ይደረጋል ተብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page