top of page

ጥቅምት  3 2018  የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የሚፈፀም ወንጀልና ህገወጥ ድርጊት ከጊዜ ጊዜ መጠኑ እየጨመረ ነው ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 21 minutes ago
  • 1 min read
ree

ይህንኑ ለመከላከል የተሟላ የህግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡


ይህን ያለው ፍትህ ሚኒስቴር ነው።


ኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ደህንነትን በተመለከተ የተሟላ የህግ ማዕቀፎች እንደሌላትም ተነግሯል።


በማህበራዊ ሚዲያ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ህገወጥ ድርጊቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰም ተነግሯል።


ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠርም ሆነ ለመከላከል የሚያስችል ድንጋጌ እንደሌለም ተናግሯል።


የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ እና ደህንነት ላይ የህግ ቁጥጥሩ ክፍተት በመኖሩ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እንዲንሸራሸሩ፣ ህገወጥ ድርጊቶችና ወንጀሎች በአደባባይ እንዲፈጸሙ በር መክፈቱን ይናገራሉ።


ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ የተሟላም ባይሆንም  የህግ ማዕቀፎች አሉ የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታው ተቋማት ፍትህን እና ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ በጋራ መስራት ላይ ክፍተት አለ ብለዋል።


እነዚህን እና መሰል የማህበራዊ ሚዲያ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተቋማት አብሮ መስራት ይገባቸዋል ይላሉ።


በተቋማት በኩል የሚደረጉ የምርመራ ስራዎች በተደራጁና ዘመናዊ በሆኑ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች የተደገፉ መሆን አለበት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ በላይሁን የፌዴራል ፖሊስ አሁን ላይ እየሰራ ያለውን ስራ በበጎ ምሳሌነትም አንስተዋል።


ሚኒስትር ዴኤታው ሰዎች ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው የሚፈጽሟቸውን ወንጀሎች እና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን መከላከልና መቆጣጠር የሚቻለውም መቀየርና መሻሻል ያለባቸውን የህግ ማዕቀፎች በማሻሻል፣ የህግ ማዕቀፎች የሌላቸውን ደግሞ የህግ ማዕቀፍ በማበጀት እንደሆነም ይናገራሉ።


የፋይናንስ ዘርፉ ለእነዚህ ወንጀሎች ተጋላጭ ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ባንኮችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትም አሰራራቸውን መፈተሽ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... https://tinyurl.com/aba284vf


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page