top of page

ታህሳስ 7/2018ሆሞ ኢሬክትስ በመባል የሚታወቀው የቅድመ ሰው ዝርያ የራስ ቅልና የፊት አጥንቶች ሙሉ ገፅታን ማወቅ መቻሉን ተነገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • 9 minutes ago
  • 1 min read


ይህም የሆነው ከ5 ዓመት በፊት በአፋር ክልል ጎና ተብሎ በሚጠራው መካነ ጥናት የተገኘው የሆሞ ኢሬክትስ ቅሪተ አካል በሳይንቲስቶች በቨርችዋል ዲጂታል ሪኮንስትራክሽን ተገጣጥሞ በተገኘ ውጤት መሆኑን ምርምሩን ያደረጉት ስለሺ ሰማው (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

ree

ለዚህ ጥናት መነሻ የሆነው ቅሪተ አካል ያገኙትም ስለሺ ሰማው(ዶ/ር) እና ማይክል ሮጀርስ(ዶ/ር) በመሩት የምርምር ስራ ነው፡፡


በጎና ፓሊዎአንትሮፖሎጂ የጥናት ፕሮጀክት እድሜው 1.5 ሚሊዮን ዓመት እንደሚደርስ የተገመተ ሆሞ ኢሬክትስ በመባል የሚታወቀው የቅድመ ሰው ዝርያ ጭንቅላት ነበር የተገኘው ብለዋል ስለሺ ሰማው(ዶ/ር)፡፡


ከዚህ ቀደም የሆሞ ኢሬክትስር የሰው ዝርያ በአዝጋሚ ለውጥ እስያ ውስጥ ከተለወጠ በኋላ ነው አፍሪካ የገባው ተብሎ የተሰራው ጥናትም ይህ የምርምር ውጤት ሀሰት መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል ተመራማሪው፡፡


ዶ/ር ስለሺ ሰማው እንደሚሉት ሆሞ ኢሬክትስ የተባለው የሰው ልጅ ዝር አርሊ ሆሞ ከሚባል ዝርያ  አፍሪካ ውስጥ አዝጋሚ ለውጥ በማድረግ ነው ሆሞ ኢሬክትስ የሆነው፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጊዜያት እየተደረገ ባለው ጥናትና ምርምር ከ6 ሚሊዮን እስከ 10 ሺ አመት ድረስ እድሜ ያላቸው የሰውል ልጅን አመጣጥን የሚያሳዩ ቅሪቶች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡


የጎና ፕሮጀክት የምርምር ውጤት በኔቸር ኮሚኒኬሽን ጆርናል ታትሞ በዛሬው እለት ይወጣል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page