ጥቅምት 27 2018 - ''በሀይማኖት ሽፋን ግጭት ለመቀስቀስ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ከድርጊታችሁ ታቀቡ ልንላቸው ይገባል'' የአዲስ አበባ ከተማ የኮሙኒኬሽን ቢሮ
- sheger1021fm
- 17 minutes ago
- 1 min read
በሀይማኖት ሽፋን ስም ግጭት ለመቀስቀስ የሚንቀሳቀሱ አካላትን "ከድርጊታችሁ ታቀቡ" ልንላቸው ይገባል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ተናገረ፡፡
የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ የከተማዋ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከሃይማኖት ሚዲያዎች የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በሰላም ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማዋ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ ሚዲያ ሰላምን ለመስበክ፣ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጠናከር ድርሻው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ይሁንና አንዳንድ ግለሰቦች ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ በማህበረሰብ መካከል ግጭት እና ቅራኔ ለመፍጠር እንደሚሰሩ ተናግረው እነዚህን አካላት በቃ ልንላቸው ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጻሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው የሃይማኖት ሚዲያዎች በተከታዮቻቸው ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳላቸው ተናግረው ይህን ቅቡልነት ሰላም ሊያሰፍን፣ መራራቅ ሳይሆን መቀራረብን በሚያመጣ መልኩ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








