ጥቅምት 20 2018 የዳሸን ሱፐር አፕ ደንበኞች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ባንኩ ተናገረ።
- sheger1021fm
- 28 minutes ago
- 1 min read
የዳሸን ሱፐር አፕ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ደንበኛና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዕለታዊ የገንዘብ ዝውውር እየተፈፀመበት ይገኛል ሲለሰ ባንኩ ከላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡
ይህንን በዛሬው ዕለት በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትና የሥራ ክፍሎች የእውቅና አሰጣጥና የፓናል ውይይት መርሃግብር መዘጋጀቱም ተጠቅሷል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ፣ ዳሸን ሱፐር አፕ ይፋ በተደረገ አንድ ዓመት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ይኖሩታል የሚለውን ዕቅድ በዘጠኝ ወራት ብቻ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
የዳሸን ሱፐር አፕን ላበለፀገው የኤግላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ ለባንኩና ለአገር ለሚያደርገው አስተዋፅኦ አቶ አስፉው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዳሸን ባንክ ‘’ሱፐር አፕ’’ ባንኩ በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ የያዘ እና ዘመናዊ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችል ሱፐር አፕ እንደሆነ ተነግሯለታል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








