top of page

ጥቅምት 20 2018 - የኮንሶ የእርከን ስራ ላይ አደጋ መደቀኑን፣ ማህበረሰቡም የአኗኗር ዘይቤው በአሉታዊ መልኩ እየተቀየረ መሆኑን ጥናት አሳየ

  • sheger1021fm
  • 43 minutes ago
  • 1 min read

የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የኮንሶ የእርከን ስራ ላይ አደጋ መደቀኑን፣ ማህበረሰቡም የአኗኗር ዘይቤው በአሉታዊ መልኩ እየተቀየረ መሆኑን ጥናት አሳየ፡፡

 

የኮንሶ የድንጋይ እርከኖች በዩኔስኮ መዝገብ የሰፈሩ ማህበረሰቡንም ያስመሰገኑ ሆነው ዓመታት አልፈዋል።

 

ገደላማውን፣ ፈታኝ ሆነውን መልካም ምድር አካፋና ዶማ ይዘው ባህላዊ እውቀታቸውን ተጠቅመው ለእርሻ ስራ አውለውታል፡፡

 

ree

ተፈጥሮን ተንከባክበው ከትውልድ ትወልድ አስተላልፈውታል፡፡

 

በኮንሶ ምድር የሚሰራው የእርከን ስራ፤ ኢትዮጵያም መታወቂያዬ ብላ በዓለም ቅርስነት  ካስመዘገበችው 15 ዓመታት ሆኗታል፡፡

 

ዛሬ ግን እዚያ ድንጋይ እየጠረቡ፣ መሬት እየቆፈሩ የሚሰሩ እጆች፣ የሚያርሱ ወጣቶች  በአካባቢ ብዙም አይታዩም፡፡

 

ወጣቶቹ ፊታቸውን ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ሄደው ማዕድን ወደማውጣት፣ ወደ ንግድ አዙረዋል፡፡

 

በአካበባዊ በሴቶች ብቻ የሚመሩ ቤተሰቦች መብዛታቸውን፣ተማሪዎች ትምህረት እየተው መምጣታቸውን ጥናቱ አሳይቷል።

 

የማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤ እተቀየረ ቅርሱም አደጋ ላይእወደቀ መምጣቱን  ጥናት አሳይቷል፡፡

 

ይህንን ያመጣውም ቀድሞውኑ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጎዳው የኮንሶ ምድር ዛሬም የዝናብ እጥረት እየተጎዳ በመቀጠሉ ነው፡፡

 

ree

ይህንን በጥናታቸው ያረጋገጡትና ፎረም ፎርም ሶሻል ስተዲስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ጥናታቸውን ያቀረቡት  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ትርሲት ሳህለ ድንግል(ዶ/ር) ናቸው፡፡


ንጋቱ ሙሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 
ጥቅምት 20 2018በፋብሪካ የተቀነባበሩ እንዲሁም ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት የሚደርሱ የጤና ጉዳቶች ኢትዮጵያን ብዙ ወጪ እያስወጣት ነው ተባለ።

ሀገሪቱ በዚህ በየዓመቱ ከ31 ቢሊየን ብር በላይ ታወጣለች ተብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለወጠ የመጣው የአመጋገብ ሥርዓት ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ጫና ከ52 በመቶ በላይ እንዲሆን ማድረጉ ተነግሯል። ይህንን ያስቀራል በሚል በዝግጅት ላይ ያለውን ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ ምግቦችን የሚቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page