ጥቅምት 20 2018 - በሶስት ወር ውስጥም ከ270 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪ ሾፌሮች መቀጣታቸውም ሰምተናል፡፡
- sheger1021fm
- 38 minutes ago
- 1 min read
በአዲስ አበባ የመንግስት ወይም 4 ቁጥር የለጠፋ ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግ እየተላለፉ አስቸግረውኛል ሲል የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ተናገረ፡፡
በሶስት ወር ውስጥም ከ270 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪ ሾፌሮች መቀጣታቸውም ሰምተናል፡፡
ኮድ 4 መኪና አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግን በመጣስ፣ እንደፈለግን እንሁን ማለታቸው ትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር ስራውን በሚያከናወንበት ጊዜ እንቅፋት እንደሆኑበት ቢሮው አስረድቷል።
በአዲስ አበባ ትራፊክ ማነጅመንት የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው ኢቴሳ ህግን ለማስከበር መነሻው ህግ ነው፣ በህግ ፊት ደግሞ ሁሉም እኩል ነው ቢባልም አንዳንድ ባለስልጣናት ግን እንደፈለጉ ባልተፈቀደ መንገድ ያሽከረክራሉ፣ በተቃራኒ መንገድ ይነዳሉ ብለዋል፡፡
ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተሰመረ መስመር ጭምር ማሽከርከር ይመርጣሉ ይህ ድርጊታቸው ደግሞ ለትራፊክ አደጋ መከሰት ጭምር ምክንያት እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ህግን ፣የትራፊክ መብራትን በሚጥሱና ባልተፈቀደ መንገድ የሚያሽከረክሩ በለስልጣናትንም ሆነ ማንኛውንም አሽከርካሪ የሚቻለውን እየቀጣን ፣ ጥሶ የሄደውን ታርጋ ቁጥሩን መዝግቦ በመያዝ በሚመለከተው አካል በማስጠራት ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ሲሉ አቶ አያሌው ኢቴሳ ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ገዛ ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








