top of page

ጥቅምት 19 2018  - ግብፅ በናይል ወንዝ ያላትን ጥያቄ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ተቀብላ በጋራ ብታቀርብ ይበጃታል ተባለ። 

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ግብፅ በናይል ወንዝ ዙሪያ ያላትን ጥያቄ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ተቀብላ በጋራ ብታቀርብ ይበጃታል ተባለ። 

 

የናይል የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት በሰፊው ወደ የሀይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ እየገቡ ነው ተብሏል። 

 

ይህንን ያሉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ናቸው። 

 

2ኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት በሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀምሯል። 

 

በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ለኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ድንበር መለያ ሳይሆኑ መተሳሰሪያ ድልድይ ናቸው ብለዋል። 

 

ree

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) የኢትዮጵያን መንገድ ተከትለው የናይል ተጋሪ የላይኛው የተፋሰሱ ሀገራት በስፋት ወደ ሀይል ማመንጫ ግንባታ እየገቡ መሆኑን አንስተዋል። 

 

ይህም ናይልን  በጋራ የመጠቀም  ሀሳብን በተመለከተ ተባብሮ መስራት የግድ እንዲል ያደርጋል ብለዋል። 

 

ባለፈው ዓመት ወደ ተግባር የተሸጋገረው የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት(ሲ.ኤፍ.ኤ) ከጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም  ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ግብፅና ሱዳን ግን አሁንም ወደ ስምምነቱ መምጣት አልቻሉም። 

 

ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ.ር) የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ብዙ ፕሮጀክት መስራት መጀመራቸውን በማንሳት ለግብፅ የተሻለው መንገድ ወደ ስምምነቱ መምጣትና ጥያቄዋን በጋራ ማቅረብ ነው ብለዋል። 

 

የህዳሴውንግድብ ተገንብቶ መጠናቀቅ ተከትሎም ከግብፅ በኩል እየቀረበ ያለው ውንጀላ ከዚህ በውሃላ ብዙም የማይጠቅምና ከንግግርም የሚሻገር እንደማይሆን አንስተዋል። 

 

በኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ የተገኙት የኬንያ የውሃ፣የንፅህና አጠባበቅና የመስኖ ሚኒስቴር ተወካይ ኢንጂነር ሳሙኤል አሊማ ሀገራቸው በመጪው ዓመት 50 የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ ለመጀመር እየተሰናዳች መሆኑን ተናግረዋል። 

 

ኢትዮጵያ አሁን ካላት የኤሌክትሪክ ሀያል አቅም 92 በመቶው ከውሃ የሚገኝ ሲሆን ከፀሀይ፣ከነፋስና ከእንፋሎት ተጨማሪ ሃይል በማመንጨት ድርሻውን የማሰባጠር ስራ የመስራት ፍላጎት ስለመኖሩ ሲነገር ሰምተናል። 

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ቴዎድሮስ ወርቁ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page