ጥቅምት 19 2018 - ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ከተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
- sheger1021fm
- 8 minutes ago
- 1 min read
ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎቸን የተግባር ላይ ልምምድ ለመስጠት አንዲሁም መምህራኑን ለማሰልጠን የመግባቢያ ስምምነት ከኮሌጁ ጋር ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን የኮሌጁ ዲን ተስፋዬ አድማሱ(ዶ/ር ) እና ትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ በመወከል Guo ZhongLei ተፈራርመውታል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ኢንፊኒክስ ክለብ በተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ይቋቁማል፣ ይህም ለተማሪዎች ለተግባራዊ የኢንዱስትሪ ልምድ፣ ለክህሎት ግንባታ እና ለፈጠራ ፍለጋ እድሎችን ይሰጣል ተብሎለታል።
በዚህ ትብብር ተማሪዎች በግል እና ሙያዊ እድገት ላይ ያተኮሩ ስለጠናዎቸን እና የማማከር ፕሮግራሞች ውስጥ ይሳተፉሉ፣ በኢንፊኒክስ እና ትራንሽን ባለሙያዎች የፈጠራ ተነሳሽ ትምህርት ይሳተፉሉ።

ከዚህ በተጨማሪም የኮሌጁ ተማሪዎች በትራንሽን እና ኢንፊኒክስ ውስጥ የስራ ዕድል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
እንዲሁም መምህራን የቴክኖሎጂ ስልጠና ያገኛሉ፣ ይህም ትምህርታቸው ከአዳዲስ የኢንዱስትሪ አዝማሚያዎች እና ልምዶች ጋር ወቅታዊ እዲያደርጉ ያግዛል ተብሎ ተነግሯል፡፡
የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ተስፋዬ አድማሱ(ዶ/ር ) “ስምምነቱ ወጣቶችን በትምህርት፣ በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ለማበረታታት ያግዛል" ብለዋል፡፡
ትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ በመወከል የተናገሩት Guo ZhongLei "ትብብሩ ለተማሪዎች የአካዳሚክ ትምህርትን ከሙያዊ ልምድ ጋር የሚያገናኙ የኢንዱስትሪ ግንዛቤዎችን፣ መመሪያዎችን እና ስልጠናዎችን እንደሚሰጥም " ጠቁመዋል።
በትራንስሽን ማኑፋክቸሪንግ ባለቤትነት የተያዘው ኢንፊኒክስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ 14 አመት የሞላው ሲሆን የቅንጡ ስልኮችን በማማረት ይታወቃል፡፡
ከኢንፊኒክስ ጋር በጋራ ለመስራት የተፈራረመው ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከ80 ዓመታት በላይ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጅነሪንግ፣ ንግድ እና ተግባራዊ ሳይንስ ትምህርቶችን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
በሌላ በኩል የኢንፊኒክስ ደንበኞቹን ከተለያዩ የኢንፊኒክስ ምርቶች ጋር ለማስተዋወቅ እና በአዲሶቹ ቴክኖሎጂዎች የተግባር ልምድ ለማቅረብ ያለመ ወርሃዊ ዝግጅት 6ኛውን የኢንፊኒክስ ቀንን አክብሯል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








