top of page

ጥቅምት 19 2018 - ኢትስዊች ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ከአንዱ ባንክ ወደ ሌላኛው ባንክ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ በአንደኛው ባንክ ካርድ በሁሉም መጠቀም የሚያስችል ስርዓት የዘረጋው #ኢትስዊች ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ።


ትርፉ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ34 በመቶ ብልጫ እንዳለው የኢትስዊች የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳሲ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል።


ይህንንም ተከትሎ የ1,000 ብር አክሲዮን የትርፍ ድርሻ 486.4 ብር ደርሷል ተብሏል።

ree

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ በአጠቃይ 2.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱንም ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 በመቶ ጭማሪ እንዳለው የቦርድ ሰብሳቢው ጠቅሰዋል።


ይህም የሚያሳየው የኩባንያው ትርፋማነት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱን ነው ሲሉ አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል።


ኢትስዊች በበጀት ዓመቱ ብዛቱ 287.4 ሚሊዮን ግብይት፣ የብር መጠኑ 741.1 ቢሊዮን የሆነ እርስ በእርሱ ተናባቢ የሆነ አገልግሎት መስጠቱ ተጠቅሷል።


ከዚህ ውስጥ 577.7 ቢሊዮን ብሩ ከአንድ የፋይናንስ ተቋም ወደ ሌላኛው የፋይናንስ ተቋም የተላለፈ ነው ተብሏል።


በተመሳሳይ እርስ በእርሱ ተናባቢ በሆነው የኤቲኤም አገልግሎት 156.1 ቢሊዮን ብር መገላበጡም ተነግሯል።


ይህ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ26 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።


የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል ሰኔ 30 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2.56 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተጠቅሷል።

ree

በፋይናንስ ተቋማት መከካል የሚደረጉ ክፍያዎቸን ተናባቢ ማድረግ፣ የሀገር ውስጥ የክፍያ ስርዓትን ማቅረብ፣ የብሔራዊ የክፍያ ጌት ዌይ አገልግሎት መስጠት፣ ለዲጂታል ክፍያዎች ሂሳብ የማጣራትና የማወራረድ የማዕከላዊ አገልግሎት መስጠትና ለፋይናንስ ተቋማት የጋራ ስርዓት መዘርጋት ስራዎቹ የሆኑት ኢትስዊች የባለፈው ዓመት ስራ ክንውኔ በብዙ መለኪያዎች ስኬታማ ነበር ብሏል፡፡


ኢትስዊች በሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሩ ባንኮች (የግል እና የመንግሥት)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት፣ የክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተሮችና የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪዎች በጋራ የተቋቋመ ነው።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page