top of page

ጥቅምት 17፣2016 - ብሪቲሽ ካውንስል ለመምህራን ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተሰምቷል

ጥያቄ ውስጥ የገባው የመምህራን ብቃት ከትምህርት ጥራት መውደቅ እና ከተማሪዎችም ውጤት ማነስ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት አለው፡፡


መምህራን አለባቸው ከተባሉ ክፍተቶች መካከል የሆነውን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃት ለማሻሻል ብሪቲሽ ካውንስል እስከ 8ተኛ ክፍል ለሚያስተምሩ መምህራን ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተሰምቷል፡፡


የትምህርት ሚኒስቴርም መምህራንን ብቁ ለማድረግ ከመጭው ክረምት ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ማሰልጠን እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡


በረከት አካሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page