top of page

ጥቅምት 14 2018 - የባንክ ደንበኞች ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ ከሰጣቸው ሂሳብ ውጪ በግላቸው ሂሳብ ግብይቶች እንደሚገላበጥ ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Oct 24, 2025
  • 1 min read

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የባንክ ደንበኞች ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ ከሰጣቸው ሂሳብ ውጪ በግላቸው ሂሳብ የተለያዩ ግብይቶች እንደሚገላበጥ ተሰማ።


ይህን ያረጋገጠው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ ነው።


ባንኩ ባደረግሁት ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ግለሰብ ነጋዴዎች በዚህ እንቅስቃሴ እንዳሉ አውቄያለሁ ብሏል።


#የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ባንክ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች የግብር ሰብሳቢ ተቋም ካስመዘገቡት የባንክ ሒሳቦች ውጪ ወደ ግል እና ሶስተኛ ወገን የገንዘብ እንቅስቃሴዎች እየፈፀሙ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ይህ አሰራርም ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣናት ቁጥጥር እና ክትትል ለመሸሽ የሚደረግ ተግባር እንደሆነ ባንኩ አስረድቷል።


በተጨማሪም በዚህ መልኩ የሚፈፀሙ የፋይናንስ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች የወንጀል ፍሬ ሊሆኑ እንደሚችሉ ባንኩ ከላከልን መግለጫ ተመልክተናል።


እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ጋር የተያያዙ ወይም የተገናኙ ሊሆኑ እንደሚችሉም ባንኩ አሳስቧል።


የፋይናንስ ሥርዓቱ ጤናማ እና ታማኝ እንዲሆን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ደህንነቱንም ለመጠበቅ ሲባል ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም ባንኮች ለንግድና ህገወጥ ድርጊት የሚጠቀሙ ደንበኞች አስመልክቶ መረጃዎችን እያደራጁ እንዲልኩ መመሪያ ማስተላለፋን ሰምተናል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page