top of page

ጥቅምት 14 2018 - ሕብረት ባንክ ከሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሰበሰበውን 35 ሚሊየን ብር   ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አበረከተ

  • sheger1021fm
  • 9 hours ago
  • 1 min read

35 ሚሊዮን ብሩ የተሰጠው ለ10  የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ነው፡፡


ድጋፍ የተርገላቸው አስሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተመረጡት በሸሪዓው መርህ መሰረት የሚሰሩ መሆናቸው ተመዝኖ፣ ከሚደርሱት የሕብረተሰብ ቁጥር እና የሚሰጠውን ድጋፍ ለምን ተግባር እንደሚያውሉትም ጭምር ታይቶ ነው ተብሏል።


ድጋፉ ከተደረገላቸው ድርጅቶች መካከል፤ እማሙ ማሊክ ትምህርት ቤት፣ ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽ፣ ባቡል ካኸር፣ ሜቄዶኒያ፣ ቢላሉ ሀበሺ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሞያዎች ማህበር ይገኙበታል።


ሕብረት ባንክ የሸሪዓውን መርህ በተከተለ መልኩ ከወለድ ነፃ የባንክ እገልግሎት መስጠት ከጀመረ 10 ዓመታት እንዳለፈው አስታውሷል።

ree

በአሁኑ ሰዓትም ሕብረት ባንክ 23 ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎች ከፍቼ እየሰራሁ ነው ሲል  ጠቅሷል።


ባንኩ ሸሪዓው በሚያዘውና የሕብረት ባንክም እንዱ እሴት የሆነውን የመረዳዳት ወይም ማሀበራዊ ሃላፊነትን የመወጣት ተግባር ለመከወን  ሕብረት ከሚሰጠው የባንክ አገልግሎች በሻገር በማሕበረሰቡ ሕይወት ውስጥ በጎ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ  ማሕበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ሲደግፍ መቆየቱን አስታውሷል።


ትናንት ምሽት በሸራተን ሆቴል በተካሄደው ድጋፍ መስጠት ዝግጅት ላይ የሴቶችና የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ ሌሎች የመንግስት ሹመኞች እንዲሁም የባንኩ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page