top of page

ጥቅምት 13 2018 - የቴክኒክ ሞያ ዘርፎች ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ትኩረት እያገኘ አይደለም ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ለሀገር እድገት መሰረት የሆኑ የቴክኒክ ሞያ ዘርፎች ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ትኩረት እያገኘ አይደለም ፤ ይህም መስተካከል አለበት ተባለ፡፡


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤና ትምህርት ማዕከል መምህር አቶ ፍስሃ ተክሉ በልጅነት የሚሰራው ስራ ነገ በቴክኒክና ሞያ ትምህርት ቤት ውስጥ እጁ ከታች ጀምሮ የተፍታታ ተማሪ እንድናገኝ ይረዳል ብለዋል፡፡


እነዚህ ተማሪዎች ከሰዎች ጋር አብሮ የመስራትና የፈጠራ አቅማቸውም እጅግ የላቀ እንዲሆን ያደርጋልም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ree

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር ታምሬ አንዷለም በበኩላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ለቴክኒክና ሞያ ትምህርት የሚሰጠው ትኩረት እጅግ አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ፡፡


የትኩረት ማነሱ ችግር ዛሬ የመጣ ሳይሆን ቀደም ካለው ጊዜ ጀምሮ የነበረ ነው ያሉ ሲሆን ለሞያ ዘርፍ ይሰጠው የነበረው አመለካከት እጅግ የተሳሳተ እንደነበር አብራርተዋል፡፡


ተማሪዎችም ቢሆን በቴክኒክና ሞያ ተቋማት ገብቶ መሰልጠን ጥሩ ባለሞያ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን እንዲያውቁ ማድረግ ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡


በዚህ ዓመት ብቻ በቴክኒክና ሞያ ዘርፍ 454,000 ተማሪዎችን ለማሰልጠን ዝግጅት መደረጉን ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ ….

በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


2 Comments



Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page