top of page

ጥቅምት 11 2018 የኢትዮዽያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ አለም አቀፍ ኩባንያ ለመሆን ጉዞ ጀምሬያለሁ አለ።

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 2 min read

ኮርፖሬሽኑ በበፊቱ አዋጅ መሰረት ሶስት የተሰጡትን ግዙፍ የኢንቨስትመንት ክንውኖችን ለመፈፀም ወደ ስራ መግባቱን ተናግሯል።


ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እፈፅማቸዋለው ካላቸው ግዙፍ ስራዎች፤ አንደኛው የምድር ባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ፤ ሁለተኛ የተገነባውን የባቡር ልማት ማከናወን እና ሶስተኛው የመሰረተ ልማት አካል አስተዳደርና ተዛማጅ ስራዎች ናቸው።


ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በተጨማሪም በአዋጅ በተሰጠው በደረጃ አንድ ኮንትራክተር ፤ በደረጃ አንድ መልቲሞዳል አገልግሎት እንዲሁም በደረጃ አንድ የባቡር አካላት ማምረቻ እና ሌሎች ፈቃዶች ወደ ስራ ለመግባት ማሰቡን ሲናገር ሰምተናል።


የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሸን ዛሬም የመንግስትና የግል ሽርክና በማስማማት ፋይናንስ ለማሰብሰብ ሲመክር ውሏል።


ኮርፖሬሽኑ እነዚህን ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለማልማት በሽርክና ማህበር በጋራ ለማልማት እና ኢንቨስትመንት አድራጊዎች ወደ ሀገር ቤት ገብተው እንዲሰሩ ለመሳብ እራሱን አስተዋውቋል።

ree

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሸን ዋና ሰራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው ከእነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ባለፈ የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናቀቅ በመንገድ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።


ኮርፖሬሽኑ ዛሬ ባደረገው ጉባኤ እይታውን አስፍቶ ወደ ግሩፕ ለማደግ በተናገረበት ወቅት የሚሰራቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አስተዋውቋል።


ከእነዚህም መካከል ግዙፍ ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ማከናወን ፤ ሆቴል እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ የሽያጭ እና ሌሎች ግዙፍ ግንባታዎችን ለመፈፀም እራሱን እያሰፋ መሆኑን አስረድቷል።


ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በለገሀር አካባቢ ባለው ሰፊ የኮርፖሬሸኑ ዋና መስሪያ ቤት ግቢ እንደሚታነፅ ሰምተናል።


የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚንስትር ድኤታ ዴንጌ ቦሩ የተለያዩ ግዙፍ መሰረተ ልማቶችን እየገነባን በተለይ በምድር ባቡር ንጣፍ ሁሉንም የኢትዮጵያ ክፍል በሁሉም ማዕዘን ለማገናኘት እንሰራለን ብለዋል።


በተያያዘም የገቢ ወጪ ጭነት በተሽከርካሪ ማጓጓዝ አድካሚ ነው ያሉት ዴንጌ ቦሩ በሎጅስቲክስ አፈፃፀም በአለም የንግድ ሥርዓት ተወዳዳሪ ለመሆን ፈተና ነው ብለዋል።


በመሆኑም የተንዛዛ እና ግዜ የሚበላ የተሽከርካሪ የሎጀስቲክስ መስመር በማስቀረት እና ወደ ባቡር ለመተካት በብርቱ መስራት እንደሚያስፈልግ ሰምተናል።


ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ኢትዮጵያ በአመት በባቡር መሰረተ ልማት የምታጓጉዘውን 2.2 ሚሊየን ቶን በመጨመር ዘንድሮ የጭነት ማመላለሱን በእጥፍ ለማድረግ መታሰቡን እግረ መንገዱን ሲናገር ሰምተናል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page