ጥቅምት 11 2018 - ባህርዳር እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በኒኩለር ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪ ት/ት መስጠት መጀመራቸውን ተናገሩ
- sheger1021fm
- 5 minutes ago
- 1 min read
በኒኩለር ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት መስጠት መጀመራቸውን ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ተናገሩ፡፡
ትምህርቱን እየሰጡ ያሉት ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ በ2ተኛ ዲግሪ ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ(ዶ/ር) በበኩላቸው ከሁለተኛ ዲግሪ ባለፈ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቁ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
በቅርቡ መንግስትበ ኢትዮጵያ የኒኩለር ፕላንት ለሰላማዊ መንገድ እንደሚገነባ የተናገረ ሲሆን ሁለቱ ተቋማት ለዚህ የሚሆን ባለሞያ ለማፍራት ማቀዳቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments