top of page

ጥር 8፣ 2015- የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የአገሪቱን ፖለቲከኞች በወታደራዊ ጉዳዮች ጣልቃ አትግቡብን አሉ

የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የአገሪቱን ፖለቲከኞች በወታደራዊ ጉዳዮች ጣልቃ አትግቡብን አሉ፡፡


አልቡርሃን ፖለቲከኞቹ በየራሳቸው ማህበራት ማሻሻያ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡


ወታደራዊ መሪው ፖለቲከኞቹ ይፈፅሙታል ያሉት ጣልቃ ገብነት በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡


አል ቡርሃን በበኩላችን በጦር ሀይላችን ውስጥ ፅንፈኞች ሰርገው እንዳይገቡ እንከላከላለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


በሱዳን በግልበጣ ስልጣን የያዙት የጦር አለቆች ቀደም ሲል አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለማሸጋገር ከተለያዩ የፖለቲካ ወገኖች ጋር ስምምነት ፈርመዋል፡፡


ሽግግሩ ለ2 አመታት እንደሚዘልቅ ታውቋል፡፡


ስምምነቱ ቢፈረምም ሱዳን አሁንም ከፖለቲካዊ ቀውሷ እንዳልተላቀቀች ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page