top of page

ጥር 6፣ 2015- የእስራኤሉ ተሰናባች ልዩ ኤታ ማጆር ሹም ሌተና ጄኔራል አቪቭ ኮቻቪ ኢራን በጥቂቱ አራት የኒኩሊየር ቦምቦችን መስራት የሚያስችላትን ዩራኒየም


የእስራኤሉ ተሰናባች ልዩ ኤታ ማጆር ሹም ሌተና ጄኔራል አቪቭ ኮቻቪ ኢራን በጥቂቱ አራት የኒኩሊየር ቦምቦችን መስራት የሚያስችላትን ዩራኒየም ማብላላቷን ተናገሩ፡፡


ተሰናባቹ ኤታ ማጆር ሹም የእስራኤል ጦር ቀደም ሲል የኢራንን የኒኩሊየር መርሐ ግብር ለመደምሰስ መላ ሲመታ ቆይቷል ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡


ዒላማዎችንም መለየቱን ተናግረዋል፡፡


የኮቻቪ የሀላፊነት ጊዜ እያበቃ ነው፡፡


እስራኤል እና ምዕራባዊያን ኢራን የኒኩሊየር የጦር መሳሪያ ለመገንባት እየተሯሯጠች ነው ይሏታል፡፡


ኢራን በበኩሏ መርሐ ግብሬ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ እና ለሰላማዊ አገልግሎት የታለመ ነው ባይ እንደሆነች ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page