top of page

ጥር 6፣ 2015- የማዕድን ሚኒስትሩን አቶ ታከለ ኡማ እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ 4 ሚኒስትሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ

  • Jan 16, 2023
  • 1 min read

የማዕድን ሚኒስትሩን አቶ ታከለ ኡማ እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ 4 ሚኒስትሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡


የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯን ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን፣ የማዕድን ሚኒስትሩን አቶ ታከለ ኡማ፤ የግብርና ሚኒስትሩን አቶ ኡመር ሁሴን እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ ሸኝቷቸዋል።


በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።


የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱንም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው ተመኝቷል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስትር ጽ/ቤት ተናግሯል።


አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በቅርቡ በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት መሾማቸው ይታወሳል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page