top of page

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

  • May 25
  • 1 min read

ግንቦት 17/2018


የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡


አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመሪያው እንደሆነ ነግሮናል፡፡

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች ከ322 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ተናገረ፡፡


አገልግሎቱ የ90 መስሪያ ቤቶችን 271 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ለመንግስት ገቢ የሆነ ገንዘብ እንደሆነ ተጠቅሷ ።


በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች ይህን ያህል ገቢ በዘጠኝ ወር ጊዜ ውስጥ ሲገኝ በአገልግሎቱ ታሪክ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።


ተቋማት አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን ማስወገድ እንዳለባቸው እና ለዚህ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ማሟላት እንዳለባቸው ለማድረግ ፤ የተሰራው ስራ ውጤቱ እንዲገኝ ማስቻሉን የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ጎጃም ታደለ ነግረውናል።

የተሰራው ስራ በየመስሪያ ቤቱ ለአርባ እና ሃምሳ ዓመታት ተከማችተው ይታዩ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር እንዲቀንስ እያደረገ ነውም ብለዋል።


ተሽከርካሪዎችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶችን አገልግሎቱ በሽያጭ ሠምተናል።


ንብረቶቹን ሲጠቀሙ የነበሩ የፌዴራል ተቋማት እና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ንብረቶቹ ይወገዱሉን ብለው ለአገልግሎቱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ስራው እንደሚከወን ወይዘሮ ጎጃም ነግረውናል


አገልግሎቱ በኤሌክትሪክ ዕቃዎች አወጋገድ ዙሪያ በቅርቡ የጀመረው አዲስ አሰራር እንዳለም ከስራ አስፈጻሚዋ ሠምተናል።


እነዚህ ንብረቶች ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፍቃድ ባገኙ ተቋማት አማካይነት እንዲወገዱ ማድረግ ጀምረናል ብለዋል።


አገልግሎቱ በሙሉ የበጀት ዓመቱ በሽያጭ ከሚወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ንብረቶች ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ የማድረግ ዕቅድ ይዟል።


በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ 9 ወራት በኤሌክትሮኒክስ የግዥ ዘዴ ለማዕቀፍ ስምምነት ዕቃዎች ግዥ ከ9.2 ቢሊየን ብር በላይ ለአሸናፊ ተጫራቾች የአቅራቢነት ምደባ ተሰጥቷል ተብሏል፡፡


ለፌዴራል ተቋማት እና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይገዛሉ የተባሉት እነዚህ ዕቃዎች ኮምፒውተሮች ፤ የፅህፈት መሳሪያዎች ፤ የፅዳት ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ እንደሆኑ ወይዘሮ ጎጃም ነግረውናል፡፡


ንጋቱ ረጋሣ

1 Comment


sharly yang
sharly yang
Jun 02

I bookmarked this name generator after using it for a couple of projects. It’s useful when you need fresh naming ideas without spending hours brainstorming.


Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page