top of page

ጥር 6፣ 2015- በሊትዌኒያ በጋዝ ማስተላለፊ አውታር ላይ ፍንዳታ ደረሰ


በሊትዌኒያ በጋዝ ማስተላለፊ አውታር ላይ ፍንዳታ ደረሰ፡፡


አውታሩ ወደ ጎረቤት ላቲቪያም ጋዝ የሚያስተላልፍ እንደሆነ ዘ ኒውዚላንድ ሄራልድ ፅፏል፡፡


የማስተላለፊያ አውታሩ እንደፈነዳ ከፍተኛ ቃጠሎ ተቀስቅሶ እንደነበር በዘገባው ተጠቅሷል፡፡


ነበልባሉ ከመሬት እስከ 50 ሜትር ከፍታ ሲወረወር ነበር ተብሏል፡፡


በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ታውቋል፡፡


በአቅራቢያው ሕንፃዎች የሚኖሩ ሰዎችን ከአደጋ ወደሚጠበቁበት ስፍራ ማውጣት እንደተቻለ ተጠቅሷል፡፡


የጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦው በምን ምክንያት ሊፈነዳ እንደቻለ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም፡፡


በጉዳዩ ላይ ምርመራ ይካሄዳል ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page