top of page

ጥር 6፣ 2015- M-23 የተሰኘው አማጺ ቡድን ከምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣ በወረራ ከያዛቸው የኢቱሪ ግዛት አካባቢዎች ለቅቆ ለመውጣት ቃል ገባ


M-23 የተሰኘው አማጺ ቡድን ከምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣ በወረራ ከያዛቸው የኢቱሪ ግዛት አካባቢዎች ለቅቆ ለመውጣት ቃል ገባ፡፡


አማፂው ቡድን ከኢቱሪ ግዛት ደረጃ በደረጃ ጠቅልሎ እንደሚወጣ ቃል የገባው ለአካባቢው ዋነኛ የሰላም አመቻች ለኬኒያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ እንደሆነ ዘ ኢስት አፍሪካን ፅፏል፡፡


M-23 ከያዛቸው ግዛቶች ለመውጣት ከመስማማቱ በተጨማሪ ተኩስ አቆማለሁ ማለቱም ተሰምቷል፡፡


ይሁንና የአማፂው ቡድን ታጣቂዎች ከያዟቸው ቦታዎች መቼ ለቅቀው እንደሚወጡ እና ከመቼ አንስቶ ተኩስ እንደሚያቆሙ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የለም፡፡


የኮንጎ ኪንሻሣ መንግስት ጎረቤት ሩዋንዳ የ M-23 አማጺ ቡድን አዝማች ነች ስትል ትከሳለች፡፡


በአሁኑ ወቅት የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አረጋጊ ሀይል በምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣ እየሰፈረ ነው፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




bottom of page