top of page

ጥር 25፣ 2015- የሩሲያ ጦር በምስራቃዊ ዩክሬይን ዳኔስክ ግዛት የምትገኘውን የባህሙት ከተማን በሙሉ ከበባ ውስጥ ማስገባቱ ተሰማ


የሩሲያ ጦር በምስራቃዊ ዩክሬይን ዳኔስክ ግዛት የምትገኘውን የባህሙት ከተማን በሙሉ ከበባ ውስጥ ማስገባቱ ተሰማ፡፡


የሩሲያ ሀይሎች ወደ ከተማዋ የሚያመራውን ዋነኛ አውራ ጎዳና ተቆጣጥረውታል መባሉን CGTN ፅፏል፡፡


የዩክሬይኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ምዕራባዊያን እና ሌሎች አጋሮቻቸው ዘመን አፈራሽ የጦር አውሮፕላኖችን እንዲያቀርቡላቸው እየጎተጎቱ ነው፡፡


ቀደም ሲል ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላ አሜሪካ አብራምስ፤ ጀርመን ደግሞ ሊዮፓርድ ታንኮችን ለዩክሬይን ለመስጠት ቃል ገብተውላታል፡፡


ዩክሬይን F-16 የጦር አውሮፕላኖች እንዲሰጧት ብትጠይቅም የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ይሄን ማድረግ አንችልም ያሉት ሰሞኑን ነው፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


bottom of page