top of page

ጥር 24፣ 2015- የብራዚል የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጂየር ቦልሶናሮ በአሜሪካ የ6 ወራት ቪዛ እንዲፈቀድላቸው ጠየቁ


የብራዚል የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጂየር ቦልሶናሮ በአሜሪካ የ6 ወራት ቪዛ እንዲፈቀድላቸው ጠየቁ፡፡


ቦልሶናሮ የመንፈቅ ቪዛ እንዲሰጣቸው ለአሜሪካ መንግስት ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠበቃቸው መናገራቸው አናዶሉ ፅፏል፡፡


እንደሚባለው ጂየር ቦልሶናሮ ደጋፊዎቻቸውን ለአመፅ በማነሳሳት በብራዚል በሕግ ይፈለጋሉ፡፡


የቦልሶናሮ ነውጠኛ ደጋፊዎች ከጥቂት ሳምንታት በፊት በርዕሰ ከተማዋ ብራዚሊያ መንግስታዊ ተቋማትን በመውረር መጠነ ሰፊ ውድመት አድርሰዋል፡፡


በቦልሶናሮ ደጋፊዎች ከተወረሩ መካከል የፓርላማው እና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕንፃ እንዲሁ ቤተ መንግስቱ ይገኙበታል፡፡


ፕሬዘዳንት ሉላ አናሲዮ ዴ ሲልቫ የአመፁ ጠንሳሾችም ሆኑ ተሳታፊዎች ሕግ ፊት ቀርበው የእጃቸውን ያገኛሉ ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



bottom of page