top of page

ጥር 23፣ 2015- የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአገሪቱ የኤሌክትሪክ መጥፋት እና መቆራረጡ ምክንያት የአደጋ ጊዜ አዋጅ የማሳወጅ እቅድ እንዳላ


የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአገሪቱ የኤሌክትሪክ መጥፋት እና መቆራረጡ ምክንያት የአደጋ ጊዜ አዋጅ የማሳወጅ እቅድ እንዳላቸው ተናገሩ፡፡


የአዋጁ መታወጅ መንግሥት ችግሩን ለማቃለል በቂ ሐብት ማሰባሰብ እንደሚያስችለው ብሉምበርግ ፅፏል፡፡


በደቡብ አፍሪካ የኤሌክትሪክ መጥፋት እና መቆራረጡ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ እየባሰበት መምጣቱ ይነገራል፡፡


በአገሪቱ ከ90 በመቶ በላይ ኤሌክትሪክ የሚያቀርበው በምህፃሩ (ኤስኮም) የተሰኘው መንግሥታዊው ኩባንያ ነው፡፡


ኩባንያው በስራ ማስኪያጃ እጥረት እና በብልሹ አሰራር እየተፈተነ ነው ይባላል፡፡


በዚያ ላይ ምዝበራ እና ያረጁ የኤሌክትሪክ አውታሮች የችግሩ ሌሎቹ ምክንያቶች ናቸው ይባላል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page