top of page

ጥር 23፣ 2015- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ዩክሬይን F-16 የጦር ጄቶችን አልልክም አሉ


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ዩክሬይን F-16 የጦር ጄቶችን አልልክም አሉ፡፡


ዩክሬይን ባለፈው ሳምንት አሜሪካ አብራምስ ታንኮችን እንደምትሰጣት ቃል ከገባችላት በኋላ F-16 የጦር አውሮፕላኖችንም ማግኘቴ አይቀርም ብላ እንደነበር ቻይና ኦርግ ድረ ገፅ ፅፏል፡፡


ባይደን ለዩክሬይን አብራምስ ታንኮችን ለመስጠት ቃል የገቡላትም ከብዙ ማቅማማት በኋላ ነበር፡፡


አሁንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬይንን እንደው በሌላ በሌላው እንረዳሻለን እንጂ F-16 የጦር አውሮፕላኖችን አንሰጥሽም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የዩክሬይን ሹሞች ከ F-16 በተጨማሪ እጅግ ዘመን አፈራሽ የሆኑ ሌሎች የምዕራባዊያን አገሮችን የጦር አውሮፕላኖችንም በእጃቸው ለማስገባት ጓጉተው እንደነበር ይነገራል፡፡


ፖላንድ ግን በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ፈቃድ ካገኘች ለዩክሬይን ዘመን አፈራሽ የጦር ጄቶችን ለመስጠት ማሰቧ ተሰምቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page