top of page

ጥር 20፣ 2015- የማላዊው ፕሬዘዳንት ላዛረስ ቻክዌራ በአገሪቱ በመዛመት ላይ የሚገኘው የኮሌራ ወረርሽኝ የአየር ለውጡ ውጤት እንደሆነ አምናለሁ አሉ


የማላዊው ፕሬዘዳንት ላዛረስ ቻክዌራ በአገሪቱ በመዛመት ላይ የሚገኘው የኮሌራ ወረርሽኝ የአየር ለውጡ ውጤት እንደሆነ አምናለሁ አሉ፡፡


የጉዳዩ ተያያዥነት ሊጠና ይገባል ማለታቸውን ቻናል አፍሪካ በድረ ገፁ ፅፏል፡፡


በማላዊ የኮሌራ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ 10 ወራት ሆኖታል፡፡


እስካሁንም ወረርሽኙ ከሺህ በላይ ሰዎች መጨረሱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡


የአሁኑ የኮሌራ ወረርሽኝ በ20 ዓመታት ጊዜ እጅግ ከባዱ ነው ተብሏል፡፡


ፕሬዘዳንት ላዛረስ ቻክዌራ የአሁኑን የኮሌራ ወረርሽኝ ከአየር ለውጡ ክስተት ጋር አያይዘው ማንሳታቸው ተሰምቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page