top of page

ጥር 17፣ 2015- የካሜሩን መንግስት ማንኛውም የውጭ ሀይል እንዲሸመግለን አንሻም አለ


የካሜሩን መንግስት ማንኛውም የውጭ ሀይል እንዲሸመግለን አንሻም አለ፡፡


በቅርቡ ካናዳ የካሜሩን ተፋላሚዎችን ለማደራደር ተሰናድቻለሁ ፤ ለዚህም የተደራዳሪዎቹን ይሁንታ አግኝቻለሁ የሚል መግለጫ አውጥታ እንደነበር ዘ ግሎብ ሜይል አስታውሷል፡፡


የካሜሩን መንግስት የውጭ ሀይሎችን ሽምግልና እና አደራዳሪነት አንሻም ማለቱ ካናዳን ኩም አድርጓታል፡፡


የካሜሩን መንግስት ጦር በአገሪቱ ሰሜን እና ደቡብ ምዕራብ ግዛቶች ከሚገኙ የመገንጠል አቀንቃኞች ጋር ሲዋጋ 7 አመታትን አስቆጥሯል፡፡


የውጭ ሀይሎችን አደራዳሪነት በጭራሽ አንቀበልም ያለው የካሜሩን መንግስት ጉዳዩ የውስጥ ችግራችን ስለሆነ ለእኛው ተውልን ማለቱ ተሰምቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page