top of page

ጥር 17፣ 2015- በአሜሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዘዳንት ማይክ ፔንስ የኢንዲያና መኖሪያ ቤት ውስን የመንግስታዊ ሚስጥር ሰነዶች ተገኙ ተባለ


በአሜሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዘዳንት ማይክ ፔንስ የኢንዲያና መኖሪያ ቤት ውስን የመንግስታዊ ሚስጥር ሰነዶች ተገኙ ተባለ፡፡


የአሜሪካ ፌዴራል የምርመራ ቢሮ (FBI) ባለሙያዎች ቀደም ሲል በፔንስ የኢንዲያና መኖሪያ ቤት ባካሄዱት ብርበራ ጥብቅ መንግስታዊ የሚስጥር ሰነዶቹ ላይ እንደረሱባቸው ዘጋርዲያን ፅፏል፡፡


በቅርቡ በአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የዋሽንግተን የግል ቢሮ እና በዴላዌር መኖሪያ ቤታቸው በምክትል ፕሬዘዳንትነታቸው ዘመን እጃቸው የገቡ የመንግስታዊ ሚስጥራት ሰነዶች መገኘታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡


እነዚህ ሰነዶች የምክትል ፕሬዘዳንትነት የሀላፊነት ዘመናቸው እንዳበቃ ለአገሪቱ ብሔራዊ መዝገብ ቤት መተላለፍ የነበረባቸው ናቸው ይባላል፡፡


ከፔንስ መኖሪያ ቤት በተገኙት ሰነዶች ጉዳይ ምርመራ መጀመሩ ታውቋል፡፡


ጆ ባይደን በቀድሞው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የአስተዳደር ዘመን፣ ማይክ ፔንስ ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ ምክትል እንደነበሩ ለትውስታ ተነስቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page