ግንቦት 26 2017 - የነዋሪዎቿም ቁጥር እያሻቀበ የመጣቸው አዲስ አበባ የከተማዋን ስፋት እና የኗሪዎቿን ቁጥር ያህል የሚመጥን የመንገድ መሰረተ ልማት ትፈልጋለች
- sheger1021fm
- 6 days ago
- 2 min read
በየጊዜው የእሰፋች የነዋሪዎቿም ቁጥር እያሻቀበ የመጣቸው #አዲስ_አበባ የከተማዋን ስፋት እና የኗሪዎቿን ቁጥር ያህል የሚመጥን የመንገድ መሰረተ ልማት ትፈልጋለች፡፡
ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የተሽከርካሪ መጠን ያላት ሀገር ብትሆንም በትራፊክ አደጋ ግን ከፍተኛውን የሞትና የአካል ጉዳት መጠን የምታስተናግድ መሆኑን ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡
ለተሽከርካሪም ይሁን ለእግረኞች የተመቸ የመንገድ መሰረተ ልማቶች መገንባት ደግሞ ይህንን አደጋ በጥፍ እንደሚቀንሰው ይነገራል፤ በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ያለው ግን ከዚህ የተለየ ነው፤ ከአመታት በፊት በዓለም አቀፍ ተቋም የተጠናና የከተማዋን መንገዶች የዳሰሳ ጥናት እንደሚለው ለመንገዶች ከሚሰጠው የኮከብ ደረጃ የአዲስ አበባዎቹ ጥቂቱን ብቻ ነው የሚያሟሉት፡፡
ይህንን ለማሻሻል ባለፉት ዓመታት የተሰሩ የመንገድ ደህንነት እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ጥቂት ማሻሻያ አላቸው አሁን ባለው የመንገዶቹ የኮከብ ደረጃ መንገዶች እስከ ሁለት ኮከብ ደርሷል የሚሉት የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ክበበው ሚደቅሳ ናቸው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው የመንገድ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ምን ይመስላል? በተለይ የእግረኞች ደህንነትን መጠበቅ ላይስ ያለው እውነታው ምን መሳይ ነው ስንል የመንገድ ደህንነት ባለሙያውን አቶ ዮሐንስ ለገሰ አነጋግረናል፤ እርሳቸው በአዲስ አበባ #ትራንስፖርት_ቢሮ የመንገድ ደህንነት ላይ የሚሰራው ዓለም አቀፉ ብሉምበርግ አስተባባሪ ናቸው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የመንገዶችን ደህንነት በተመለከተ በፊት የተጠናው ጥናት በተለይ ከእግረኞች ደህንነት ጋር በተያያዘ ያለው ውጤት ዝቅተኛ ነው ይላሉ፡፡
አሁን የተሻሻሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶች አሉ በተለይ ለእግረኞች የተሻለ የመንቀሳቀሻ አካባቢ ተፈጥሯል ነገር ግን ደግሞ በተመሳሳይ የተሽከርካሪ ፍጥነት ጨምሯል ለዚህም እግረኞችን ከአደጋ ለመጠበቅ ዘመናዊ የእግረኛ መሻገሪያዎች አሁንም ትኩረት ተሰጥቶ በተለይ ቴክኖሎጂን መሰረት ባደረገ መልኩ መገንባት አለባቸው ይላሉ፡፡
የመንገድ ደህንነት ላይ የሚሰሩ ስራዎች እግረኞችንም አሽከርካሪዎችንም ከአደጋ የሚጠብቁ ሆነው ቢሰሩ ጥቅማቸው በሀገሪቱ ኢኪኖሚ ላይ ጭምር ነው የሚሉት አቶ ዮሐንስ በዓለም ያለው ልምድም ይኸው እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡
ምንም እንኳን ጥቂቶቹ የአዲስ አበባ መንገዶች ለእግረኞች ደህንነት የተሻለ ሆነው ቢገነቡም በፍጥነት ምክንያት ግን በእግረኞች ማቋረጫ ወይም ዜብራ መንገዶች ላይ ጭምር አደጋ የሚደርስባቸው እግረኞች በመኖራቸው አሁንም የእግረኞችን ደህንነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ማተኮር እንደሚያስፈል ባለሞያው ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments