ግንቦት 11 2017 - በዓመት ከ7,000 በላይ ሰዎች በኤችአይቪ የሚያዙ ሲሆን አስር ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ይሞታሉ የተባለ
- sheger1021fm
- 2 days ago
- 1 min read
በዓመት ከ7,000 በላይ ሰዎች በኤችአይቪ ኤድስ #HIV_AIDS የሚያዙ ሲሆን አስር ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ይሞታሉ የተባለ፡፡
የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ ሆኖ የታየው በቀን ሰራተኞች በተማሪዎች እና በአጠቃላይ በማህበረሰብ ውስጥ እንዲሆንም ተነግሯል፡፡
እንደ ሀገር የስርጭት መጠኑ ከአንድ በመቶ በታች ነው ሲባል ዝቅተኛ ቢመስልም አሁን ባለበት ካልተገታ በድጋሜ ወረርሽኝ የሚባለው በደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የኤችአይቪኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ ተናግረዋል፡፡
በተለይም ደግሞ ወጣቱ ትውልድ ለበሽታ የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ እየሆነ መምጣቱ ወረርሽኝ የመሆን እድሉን ሊያሰፋው ይችላል ሲሉ ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡
በዚህም ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንዳለ እንደሚገመትም ተናግረዋል፡፡
የስርጭት መጠኑ ከክልል ክልል ይለያያል ያሉን ስራ አስፈፃሚው አዲስ አበባ መጠኑ ከፍተኛ ሆኖ ከሚታይባቸው መካከል ቀዳሚ እንደሆነችም ያስረዳሉ፡፡
ጋምቤላ፣ ሀረሪ፣ ትግራይና አማራ ክልል ከፍተኛ ስርጭት እንደሚታይባቸውም ሰምተናል፡፡
እድሜአቸው ከ15 እስከ 29 ዓመት ያሉት ወጣቶች እና ሴቶች አዲስ የመያዝ እድላቸው 70 በመቶ ነው ተብሏል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
Comentarios