top of page

ዶንኪ ድራይቭ የተሰኘ የሜትር አገልግሎት ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ።

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

ታህሳስ 8/2018


ዶንኪ ድራይቭ የተሰኘ የሜትር አገልግሎት ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ።


ሀሴት ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ማህበር ዶንኪ ድራይቭ የተሰኘ አዲስ የትራንስፖርት መተግበሪያ ወይም አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል።


ዶንኪ ድራይቭ የሜትር አገልግሎት ከመንገድ የመጫን አገልግሎትና የዋጋ ድርድር በመተግበሪያው መካተቱ፣ የጉዞ ማስጀመሩ በተሳፋሪው እንዲሆን ማድረግ መቻሉ፣ ያለ ጥሬ ገንዘብ ክፍያን በራሱ መተግበሪያ መፈፀም ማስቻሉና የብድር አገልግሎት ማቅረቡ ልዩ ያደርገዋል ተብሎለታል።


በተጨማሪም በ5 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ እንግሊዘኛ እና አረብኛ ቋንቋን ይሰራል ተብሏል።

ree

ዶንኪ ድራይቭ ሰዎችን ማጓጓዝ ብቻ ሳይሆን የዴሊቨሪ ወይንም እቃ ማጓጓዝ አገልግሎትንም ይሰጣልሲባል ሰምተናል፡፡


በሌላ በኩል ወደ ዶንኪ ድራይቭ ተቀላቅለው አገልግሎት ለሚሰጡ አሽከርካሪዎች ካለ ምንም ማስያዣ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ አሰራር መዘርጋቱንም ተነግሯል፡፡


ወደ ስራ ከገባ 6 ወራት ገደማ ያስቆጠረው የኦሮሚያ ባንክ ሚልኪ ታክሲ የፋይናንስ አገልግሎት ከዶንኪ ድራይቭ ጋር በጋራ መስራት መጀመሩን የተናገረው ባንኩ ያለምንም ዋስትና ለአሽከርካሪዎች የብድር አገልግሎቶችን እሰጣለሁ ብሏል።


አሽከርካሪዎቹ ከ5,000 እስከ 50,000 ብር ያለምንም ዋስትና ከኦሮሚያ ባንክ መበደር እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Recent Posts

See All
በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከትምህርታቸው የራቁ፣ ጎዳና የወጡ ህፃናት ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መሰናዳቱ ተሰማ፡፡

ታህሳስ 8/2018   በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከትምህርታቸው የራቁ፣ ጎዳና የወጡ ህፃናት ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መሰናዳቱ ተሰማ፡፡   በፕሮግራሙ በሚገኘው ገቢ 50,000 ህፃናት ለመደገፍ ታስቧል፡፡   የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙን ሜሪጆይ ኢትዮጵያና የሴት ጋዜጠኞች፣  ደራሲያን፣ ም

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page