top of page

በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከትምህርታቸው የራቁ፣ ጎዳና የወጡ ህፃናት ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መሰናዳቱ ተሰማ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ታህሳስ 8/2018

 

በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከትምህርታቸው የራቁ፣ ጎዳና የወጡ ህፃናት ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መሰናዳቱ ተሰማ፡፡

 

በፕሮግራሙ በሚገኘው ገቢ 50,000 ህፃናት ለመደገፍ ታስቧል፡፡

 

የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙን ሜሪጆይ ኢትዮጵያና የሴት ጋዜጠኞች፣  ደራሲያን፣ ምሁራን ጥምረት በጋራ በመሆ እንዳዘጋጁት ተሰምቷል።

 

አላማውም በችግር ምክንያት ከትምህርት ውጪ የሆኑ ልጆችን ‘’የእኔም ልጆች ናቸው’’ በሚል ልጆቹን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ስራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

ድጋፍ የሚደረግላቸው እና በጥናት የተለዩ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግር ምክንያቱ የተጎዱ የአማራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሚያ፣ የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች እንደሆኑ ሰምተናል፡፡

 

በእነዚ ክልሎች በርካታ ህፃናት በተፈጥሮና በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል ሲሉ የነገሩን ለዚሁ ተብሎ በተቋቋመው ጥምረት ውስጥ ሰብሳቢና በሞያቸው ጋዜጠኛ የሆኑት ሮማን ተገኝ ናቸው፡፡

 

በዚህም መሠረት ከጥር 20 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ በሀገር ውስጥም ይሁን በተለያዩ የዓለም ሀገራት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እነዚህን በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ህጻናትን ለመርዳት እጆቻችሁን ዘርጉልኝ ሲል ጥምረቱ ጠይቋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

 

ማርታ በቀለ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page