top of page

ዳሽን ባንክ በ2017 በጀት ዓመት 6.7 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ትርፍ አግኝቻለሁ አለ።

  • Dec 25, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 16/2018


ዳሽን ባንክ በ2017 በጀት ዓመት 6.7 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ትርፍ አግኝቻለሁ አለ።


አጠቃላይ ሃብቴም ከ254 ቢሊየን ብር ተሻግሯል ብሏል።


የባንኩ ባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።


በዚሁ ወቅት ሲነገር እንደሰማነው የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ከ202 ቢሊየን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ካፒታሉም 14 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ሆኗል።

በበጀቱ ዓመቱ 1 ነጥብ 12 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን የጠቀሰው ዳሽን ባንክ አጠቃላይ የብድር ክምችት መጠኑ በሂሳብ ዓመቱ 134 ቢሊየን ብር መድረሱን አክሏል።


አመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የታየበት እንደነበር የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ተናግረዋል።


ዳሽን ባንክ ግን በኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ መሪነቱን ያስመሰከበረት ሆኖ አልፏል ብለዋል።


የአገልግሎትና የፋይናንስ ውጤቶቻችን ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተቋቁመን እያደግን እንደምንገኝ ማሳያዎች ናቸው ያሉት ደግሞ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ ናቸው።


ዳሽን ባንክ አሁን ላይ የደንበኞቹን ቁጥር 7.88 ሚሊየን ማድረሱ የተጠቀሰ ሲሆን የቅርንጫፎቹ ብዛትም 906 ደርሷል ተብሏል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page