top of page

መጋቢት 20፣2016 - የፋሲካ ኤክስፖ ለማካሄድ ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ በ 30 ሚሊዮን ብር ማሸነፉ ተሰማ

ከሚያዝያ 5 እስከ 26 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደውልን የፋሲካ ኤክስፖ ለማካሄድ ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ በ 30 ሚሊዮን ብር ማሸነፉ ተሰማ፡፡


በኤክስፖው በአማካይ በቀን 15 ሺህ ጎብኚዎች፣ ከ500-600 አምራች፣ አከፋፋዮችና ነጋዴዎች እንደሚሳተፉ የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውገ ጀማነህ አስረድተዋል።


ንግድ ትርኢት እና ባዛሮች ሸማች እና ሻጭን በሰፊው የማገናኘት እድል ስለሚሰጡ በበጎ ጎናቸው ይነሳሉ፡፡


ዋጋ እና ጥራት ደግሞ የሚነሳባቸው ቅሬታ ነው፡፡


ሸገር በዚህ ጉዳይ ላይ የገበያ ሁነቶችን በማዘጋጀት 25 ዓመታት የሰራውን አና የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን ጠይቋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




bottom of page