top of page

የጤና ሚኒስቴር የህክምና ተቋማት የሚሰጧቸውን የተለያዩ የህክምና አይነቶች ያካተተ መተግበሪያ አስመርቋል

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

ህዳር 2 2018

 

በሀኪም የታዘዙ መድሀኒቶችን በቀላሉ ፈልጎ ማግኘት ብዙ ጊዜ ለተጠቃሚዎች ፈታኝ ይሆናል፤ አንዳንዶቹ መድሃኒቶች በተወሰኑ የመድኃኒት መደብሮች ወይም ፋርማሲዎች የሚገኙ አልፎ አልፎም በደላላ ዋጋ ተጨምሮባቸው የሚሸጡ መሆኑን ታካሚዎች ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡

 

ይህንን ያስቀራል በሚል በተጨማሪም የህክምና ተቋማት የሚሰጧቸውን የተለዩ የህክምና አይነቶች ያካተተ መተግበሪያ የጤና ሚኒስቴር ትናንት አስመርቋል፡፡

 

መተግበሪያው የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመደገፍና በተለይ ብዙ ችግር የሚታይበትን የመድኃኒት አቅርቦት ስርዓት ለማገዝ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

 

ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ መተግበሪያውን ካለሙት ባለሙያዎች አንዱ ናቸው አሁን ዲጂታል ጤናን በእንደዚህ አይነት መልኩ መጀመሩ የመድኃኒቶችን ዋጋ እና ቦታውን በቀላሉ ለማወቅ በተጨማሪም መድሃኒቱ ከተገዛ በኋላ ችግር ቢኖርበት ለመመለስም የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

 

መተግበሪያው ከመድኃኒት መደብሮች በተጨማሪ የህክምና ተቋማት የሚሰጡትን ህክምና አይነቶች ለይቶ ለተገልጋዮቹ የሚያሳውቅ ጭምር ነው የሚሉት ኢንጂነር ውብአየሁ ይህም በፍጥነት ህክምና የሚፈልጉ እንደ ስትሮክ ያሉ ህመሞችን ቶሎ ለማከምና ህሙማንንም ከከፋ ጉዳት ለመጠበቅ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

 

መተግበሪያው በተለይ በከተሞች ነዋሪ ለሆኑ እንዲሁም ዘመናዊ ስልኮችን ለሚጠቀሙ አመቺ ቢሆንም አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በገጠሩ ክፍል ነዋሪ በመሆኑ ያንን እንዴት ታሳቢ ያደርጋል በሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ባለሙያው ለሁሉም ያገለግላል ለገጠር የኢትዮጵያ ክፍል ደግሞ በአጭር ቴሌኮም ቁጥር በመደወል የሚፈልጉት በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

አዲሱ የሞባይል መተግበሪያ ሰዎች ስለ መድሀኒት አቅርቦት የጤና አገልግሎቶችና የጤና መረጃን በቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡

 

በመተግበሪያው ላይ እስካሁን ከ1700 በላይ መድሃኒት ቤቶች እንዲሁም ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ የመድኃኒት አይነቶች መመዝገባቸውን ሰምተናል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page