top of page

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሐዋርያዊ ኃላፊነታቸውን አስረከቡ።

  • 7 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 5/2018


የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሐዋርያዊ ኃላፊነታቸውን አስረከቡ።


ብፁዕ ካርናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ኃላፊነታቸውን ያስረከቡት በጡረታ ምክንያት እንደሆነ ቤተክርስቲያኗ አስታውቃለች፡፡


የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዎ 14ኛ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ላቀረቡት ከሃላፊነት የመነሳት ጥያቄ፤ በዛሬው ዕለት መቀበላቸውን በቅድስት መንበር ልዩ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ አማካይነት ይፋ መደረጉን በቤተክርስቲያኗ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል፡፡



የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ተተኪ በመሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ተሹመዋል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…









Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page