የድንበር ላይ ስልጠና ወስደው ሰርተፊኬት የሌላቸው ሰዎች፤ የሀገር ድንበር ተሻግረው መገበያየት እንዳይችሉ ሊደረግ ነው፡፡
- 23 hours ago
- 1 min read
መጋቢት 16/2018
የድንበር ላይ ስልጠና ወስደው ሰርተፊኬት የሌላቸው ሰዎች፤ የሀገር ድንበር ተሻግረው መገበያየት እንዳይችሉ ሊደረግ ነው፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለድንበር አካባቢ ነዋሪዎች የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ሥልጠና እሰጣለሁ ብሏል።
ከስልጠናው በኋላ ሰርተፊኬት የሌላቸው ሰዎች ድንበር ተሻግረው መገበያየት አይችሉም ተብሏል።
ይህ የተባለው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም (IOM) እና ከጃፓን መንግስት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁትን የድንበር ተሻጋሪ ንግድ የሥልጠና ማኑዋል ባስተዋወቁበት መድረክ ላይ ነው።

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስር እና ኤክስፖርት ፕሮሞሽን አማካሪ የሆኑት አቶ ፀጋው በለጠ፤ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ የኮንትሮባንድ ንግድ እና በድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይ ነዋሪዎች የሚገጥማቸውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት ስልጠናው አስፈልጓል ብለዋል።
አቶ ፀጋው የድንበር አከባቢ ነዋሪዎች የሚወክላቸውን ሰው ይመርጣሉ፣ የተመረጠው ሰው ስልጠና ከወሰደ በኋላ ሰርተፊኬት ይሰጠዋል፣ ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የፍጆታ ዕቃ ከጎረቤት ሃገር አምጥቶ የማከፋፈል ፍቃድ ይኖረዋል በማለት አስረድተዋል።
ሰርተፊኬቱ የሌለው ሰው የድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንዳያካሂድ ይደረጋልም ብለዋል።
ይህም ድንበር አካባቢ ያለ ማህበረሰብ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዞ ከመሃል ሃገር የሚፈልገውን ዕቃ ለመግዛት የሚወስድበትን ጊዜ እና ጉልበት ይቆጥባል፣ የኮንትሮባንድ የንግድ እንቅስቃሴዎችንም ይከላከላል ተብሏል።
አጠቃላይ የስልጠና ፕሮጀክቱ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአይኦኤም(IOM) እና የጃፓን መንግስት ድጋፍ እየተሰራ ስለመሆኑም በመድረኩ ላይ ተነግሯል።
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments