top of page

የካቲት 25 2017 - ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የምትልከው ዓመታዊ ምርት፤ ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ከምትልከው በእጥፍ ያንሳል ተባለ

  • Mar 4, 2025
  • 2 min read

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የምትልከው ዓመታዊ ምርት፤ ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ከምትልከው በእጥፍ ያንሳል ተባለ፡፡

 

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እንደ እ.አ.አ በ2023 ምርቶችን ልካ ያገኘችው ገቢ 58 ሚሊዮን ዶላር ነው የተባለ ሲሆን በተመሳሳይ ዓመት ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ምርቶቿን ልካ ያገኘችው ገቢ 112.4 ሚሊዮን ዶላር ነው ተብሏል፡፡

 

የሁለቱ ሀገራት ዓመታዊ የንግድ ልውውጥ እስካሁን 200 ሚሊዮን ዶላር መድረስ እንዳልቻለ ተነግሯል፡፡

 

ይህ የተነገረው ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያና የኬንያ የንግድ ፎረም ላይ ነው፡፡

 

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ዮሐንስ ፋንታ የኢትዮጵያና የኬንያ ዓመታዊ የንግድ ልውውጥ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ልካ በ2023 ያገኘችው ገቢ 58 ሚሊዮን ዶላር እንደማይሻገር የተናገሩት አምባሳሩ በተመሳሳይ ኬኒያ ወደ ኢትዮጵያ ከላከችው ምርት 112.4 ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች ብለዋል፡፡

 

ይህም የሁለቱ ሀገራት ካላቸው ታሪካዊ ግንኙነት አንፃር ዝቅተኛ መሆኑን አስረድተው ይህን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ በዋኝነት የምትልካቸው ምርቶች ቡና ፣ ቅመማ ቅመም ፣ የቆዳ ውጤቶች እና የኤሌክትሪክ ግብአቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

 

 ኬንያ ደግሞ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ ትልካለች ብለዋል፡፡

 

በኢትዮጵያ የኬንያ አምባሳደር ጆርጅ ኦሪና በበኩላቸው ኢትዮጵያና ኬንያ ረዥም ታሪካዊ ግንኙነት ቢኖራቸውም አመታዊ የንግድ ልውውጣቸው ግን ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡

 

ይህን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስትመንት ምቹ እንዲሆን የማክሮ ኢኮኖሚን ማሻሻያን  ጨምሮ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው ስለዚህ የኬንያ ወጣቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፀሐፊ አቶ ዘካሪያስ አሰፋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ረዥም ታሪክ እንዳላቸው ተናግረው ይህም ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ንግድ መለወጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

 

ዛሬ በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በኬኒያ መንግስት አማካኝነት የተሰናዳው የኢትዮ ኬኒያ የቢዝነስ ኮንፈረንስ   ለ5 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተነግሯል፡፡

 

ያሬድ እንዳሻው

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


 

 

 

 

Recent Posts

See All
በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ።

ሐምሌ 23 2018 በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ። በኢትዮጵያ የብሄረሰቦች ታሪክ ጥልቅ ትስስር እና መስተጋብር ያለው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የታሪክ ባለሞያዎች ማህበር ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስ

 
 
 
በ2018 በጀት ዓመት ከ1.2 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 23 2018 በ2018 በጀት ዓመት ከ1.2 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። በየዓመቱ በሀገሪቱ የሚገኘው የምርት መጠን እያደገ እንደሚመጣ ሪፖርቶች ያመልክታሉ። በገበያው ውስጥ ግን የምርት ዋጋ ከአመት አመት እየጨመረ እንጂ ሲቀንስም አይታይም። ይህ ለምን ሆነ? እውነትስ

 
 
 
እድሜያቸው ከ14 እስከ 24 የሆኑ አፍላ ወጣቶች በተለይም ሴቶች ላይ እየታየ ያለው የኤች አይ ቪኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን፣ ይህም ከፍተኛ ትኩረትእንደሚያስፈልገው ኔፕ ፕላስ (NEP+) የተባለ ድርጅት ተናገረ።

ሐምሌ 23 2018 እድሜያቸው ከ14 እስከ 24 የሆኑ አፍላ ወጣቶች በተለይም ሴቶች ላይ እየታየ ያለው የኤች አይ ቪኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን፣ ይህም ከፍተኛ ትኩረትእንደሚያስፈልገው ኔፕ ፕላስ (NEP+) የተባለ ድርጅት ተናገረ። Network of Networks of HIV Positives in

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page