top of page

የካቲት 25፣2016 - አዋሽ ባንክ ‘’የደንበኞች ሳምንት አከባበበር እና የዲጂታል ወር’’ መርሀ ግብሮችን አስጀመረ፡፡

የባንኩን ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን የደንበኞች ሳምንትን መርሐ ግብር እና ለአንድ ወር የሚቆየውን የዲጂታል ወር መርሐ-ግብር ያስጀመሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ፀሐይ ሽፈራው ናቸው፡፡


የዚህ መርሐ ግብር ዋና ዓለማ የባንኩን ደንበኞች በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚያቀርቡበት፣ ባንኩም ድክመቶቹን ተረድቶ በማረም ደንበኞቹ የላቀና ወጥነት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው ሲሉ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡


አዋሽ ባንክ ከዚህ ቀደም የሚጠቀምበትን የሞባይል መተግበሪያ ‘’የአዋሽ ብ’’ር ወደ የአዋሽ ብር ፕሮ (AwashBIRR pro) መለወጡንም አስረድቷል፡፡


ይህም መተግበሪያ ከዚህ ቀደም ደንበኞች ሲጠቀሙበት ከነበረው ‘’አዋሽ ብር’’ መተግበሪያ በእጅጉ የላቀ እና ደንበኞች በቀላሉ የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን የሚከታተሉበት፣ የአየር ሰዓት የሚሞሉበት እንዲሁም በፈለጉት ጊዜ እና ሰዓት የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን፣ የትምህርት ቤት፣ የአየር መንገድ፣ የዲ ኤስ ቲቪ፣ የካናል ፕላስ፣ የጉዞ ጎ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አገልግሎት ክፍያ፣ እና ሌሎች ክፍያዎቻቸውን የሚያከናዉኑበት መሆኑ ተነግሯል፡፡


ደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የ’’አዋሽ ብር ፕሮ’’ን መተግበሪያ ስልካቸው ላይ መጫን እና ወደ ቅርንጫፍ በመሄድ ከሂሳባቸው ጋር አሰናስነው መጠቀም ይችላሉ ተብሏል፡፡


ከ11.4 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን አሉኝ ያለው አዋሽ ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ከ 200 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠንም ከ 172 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ብሏል፡፡


ባንኩ የተከፈለ ካፒታሉን በመጪዎቹ አምስት ዓመታ ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወስኖ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ሲባልም ሰምተናል፡፡



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




bottom of page