የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገበት መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- 22 hours ago
- 1 min read
ጥቅምት 26 2018
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገበት መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
የሚከለሰው ሥርዓተ ትምህርትም በ2018 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተልዕኮ መሰረት ባደረገ መልኩ ስርዓተ ትምህርቱን የመከለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ክለሳው ያስፈለገው የቀድሞዎቹ ሥርዓተ ትምህርቶች ዘመኑን ያልዋጁና ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋር በአግባቡ ያልተቃኙ በመሆናቸው ነው ብለዋል።
አዲሱ እየተከለሰ ነው የተባለው የከፍተኛ ትምህርት፣ ሥርዓተ ትምህርት ተመራቂዎች በትምህርት ፕሮግራሞቹ ከተማሩ በኋላ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት በአግባቡ የፈተሸ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ነገዎ በበኩላቸው የሚከለሰው ሥርዓተ ትምህርት ሙያና ተግባር ተኮር መሆኑን ጠቅሰው ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ምሩቃንን ማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
በሁለት ዙሮች እስካሁን 55 የትምህርት ፕሮግራሞች መከለሳቸውን አንስተው እስከ ዓመቱ መጨረሻም ከ80 የሚበልጡ ፕሮግራሞች እንደሚከለሱ ጠቅሰዋል፡፡
አዲስ የተከለሱት የትምህርት ፕሮግራሞች በ2018 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ የገቡ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ወይም ከመጭው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረጉም ተጠቅሷል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments