top of page

የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የመሬት አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶች የአርሶአደሮች የመሬት ይዞታ መብት መጠበቅ ላይ መሰራት አለበት ተባለ።

  • sheger1021fm
  • 4 hours ago
  • 1 min read

ታህሳስ 16/2018


በኢትዮጵያ የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የመሬት አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በተለይም የአርሶአደሮች የመሬት ይዞታ መብት መጠበቅ ላይ መሰራት አለበት ተባለ።


ከመሬት አስተዳደር ጋር በተገናኘ ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል አርሶአደሩን በመሬቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል።


ይህ የተባለው 3ተኛውን የኢትዮጵያ የመሬት ቀን አስመልክቶ ላንድ ፎር ላይፍ በተባለ ሀገር በቀል ተቋም በተሰናዳ የፓናል ውይይት ላይ ነው።


ላንድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ፣ በመሬት አስተዳደር እና ኃላፊነት የተሞላበት የግብርና ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚሰራ ድርጅት ነው ተብሏል።

ree

ምክክሩ የኢትዮጵያ የመሬት አስተዳደር ተቋማዊ እና የሕግ ማዕቀፎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ፣ በፖሊሲ ጉዳዮች፣ የከተማ መሬት አስተዳደር ፣ ኃላፊነት በተሞላበት የግብርና ኢንቨስትመንት ላይ እየተካሄደ ነው።


በኢትዮጵያ አርሶአደሩ ከመሬቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በዘመናዊ መንገድ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም በተመለከተ በግብርና ሚኒስቴር በኩል ለአርሶ አደሩ ማረጋገጫ በመስጠትና በመመዝገብ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ ነው ተብሏል።


ከተሞች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መስፋፋታቸው በተለይም ለነሱ ቅርብ የሆኑ የእርሻ መሬቶች መጋፋታቸው የአርሶ አደሩን የመሬት መብት ተጠቃሚነት የሚጎዳ በመሆኑ የመሬት አስተዳደር ስርአቱ ይህንን ታሳቢ በማድረግ መስራት እንደሚጠበቅበት ተነግሯል።


ከአርብቶ አደሩ የመሬት ባለቤትነት ጋርም በተመሳሳይ የህዝብ ቁጥርና የእንስሳት ብዛት መጨመር ተከትሎ የመሬት አጠቃቀም ስርዓቱ እየተለወጠ መምጣቱን በመድረኩ ላይ በቀረበ ጥናት ተጠቅሷል።


በየክልሉ ያለው የመሬት ሀብት በአግባቡ ተመዝግቦ መሬት የግጭት መነሻ እንዳይሆንና እንዳይባክን አርሶአደሩ ከመሬቱ እንዲጠቀም በግብርና ሚኒስቴር በኩል የተጀመሩ ስራዎች ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል።


የኢትዮጵያ የመሬት ቀን አስመልክቶ በተሰናዳው የፓናል ውይይት ላይ አርሶአደሮች ፣ የክልል የግብርና ቢሮ ሃላፊዎች ፣ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎች እና መምህራን ተገኝተዋል።


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page