top of page

የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር የነበረውን የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጉን ተናገረ፡፡

  • 8 hours ago
  • 2 min read

ግንቦት 14/2018


በኢትዮጵያ ከ35 ዓመታት በፊት ጀምሮ የስነ ተዋለዶ፣የ እናቶችና ህጻናት ጤና አግልጎሎቶችን ሲሰጥ የቆየው የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ (MSI) ከፍተኛ ቁጥር የነበረውን የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጉን ተናገረ፡፡


ድርጅቱ ባለፉት 10 ዓመታት በተለይ በዓመት በአማካይ ለ2,000 ሰዎች አገልግሎቱን ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሷል፡፡


በሰጣቸው የስነ ተዋለዶ፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር አንዲያድግ አንዲሁም የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞት አንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጾ ማበርከቱን የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተሩ አበበ ሽብሩ (ዶ/ር) ነግረውናል፡፡


በዚህም ለምሳሌ ባለፈው ዓመት ብቻ ከወሊድ ጋር በተያያዘ 1000 እናቶችን ከሞት ታድገናል ብለዋል፡፡


30 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ብዙ እናቶች ከሚሞቱባቸው 4 ሀገሮች ውስጥ እንደነበረችና የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ተደራሽ አለመሆን በተለይ አገልግሎት ምቹ የሆነ ፖሊሲ ያልነበረው መሆኑ ችግሮች ነበሩ ሲሉ ሃላፊው አስረድተዋል፡፡



የእናቶችን ሞት ቁጥር ለመቀነስ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ብዙ ከወሊድ አገልግሎቶች ጋር በተገናኘ የሚሞቱ እናቶችና ህፃናት ቁጥር መቀነስ እንዲሁም የስነ ተዋልዶ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ወጣቶችን ማገዝ ላይ የተከወኑ ስራዎች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን አበበ (ዶ/ር) ይናገራሉ፡፡


በኢትዮጵያ ውስጥ ከዓመታት በፊት ከ 100,000 እናቶች 1,000 ያህሉ ከወሊድ ጋር በተገናኙ የጤና ችግሮች ምክንያት ይሞቱ እንደነበር ያነሱት አበበ (ዶ/ር) አሁን ይህ ምጣኔ ወደ 160 መቀነሱን ተናግረዋል፡፡


ይህ ለውጥ የመጣውም በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበረሰብ የሙያ ማህበራት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ነው ብለዋል፡፡


ነገር ግን ከቅርብ አመታት ወዲህ የአምአቀፍ ለጋሾዎች ድጋፍ መቀነስ በስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ላይ ተጽእኖ እያሳደረ በመሆኑ ስራዎቹ በሀገር ውስጥ ምንጭ ላይ መመስረት እንዳለባቸው አስገድዶናል ሲሉም አስረድተዋል፡፡


የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያም በራሱ ሃብት መፍጠር ላይ ለመስራት ከ5 ዓመታት በፊት በመወሰን ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል፡፡


ይሁን እንጂ ተቋሙ ከተመሠረተበት ዓላማ አንጻር ለአገልግሎት ክፍያ መጠየቁ የንግድ ተቋም አያደርገውም ወይም አንዳንዴ ቅሬታ ሲቀርብበት ይታያል ያልናቸው ዳይሬክተሩ፤ ድርጅቱ ራሱን እንዲችልና ከውጭ ድርጅቶች ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ጥገኝነቱ እንዲቀንስ ነው፤ አገልግሎት እንዳይቋረጥ በውጪ ድርጅቶች ያለን ጥገኝነት ለመላቀቅና ከአገልግሎት የሚገኘው ገቢ በመሰብሰብ መልሶ ለማህበረሰቡ ማዋል የሚያስችል አሰራር ነው የፈጠርነው ይህም በጤና ሚኒስቴር ጭምር ዕውቅና ተሰጥቶታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page