top of page

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከዚህ በኋላ ኢንዱስትሪዎች የሚገነባባቸው አካባቢዎች መሰረተ ልማት ለሟሟላት አመቺ ካልሆነ አይገነባም አለ፡፡

  • Feb 20
  • 1 min read

የካቲት 13/2018 

 

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከዚህ በኋላ ኢንዱስትሪዎች የሚገነባባቸው አካባቢዎች መሰረተ ልማት ለሟሟላት አመቺ ካልሆነ አይገነባም አለ፡፡

 

አሁን ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት በማሰብ መሬት በአንዳንድ ክልሎች ለማዘጋጀት እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

 

በተለያዩ ምክንያቶች ከዚህ ቀደም ከተዘጉ ኢንዱስትሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ ስራ ለመመለስ ተችሏል ብሏል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት የውጪ ምንዛሪ በተፈለገው ልክ አለማግኘትና ሌሎችም ችግሮች በተለያዩ ጊዜያት በአምራቾች ዘንድ ሲነሳ የነበረ ችግር ነው ብለዋል፡፡

 

መንግስት እነዚህ ችግሮችን ለመፍታት ባለፉት 4 ዓመታት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

ባለፉት 3 አማታት የተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከመጀመሩ በፊት የኢንደስትሪዎች የማምረት አቅም 46 ከመቶ ነበር አሁን ወደ 66 ከመቶ ማደጉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

 

ችግሮች አሁንም ድረስ በዘርፉ አሉ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጦች እየታየ ነው ይላሉ፡፡

 

ከዚህ ቀደም የነበረው የዘርፉ ፖሊሲ ሁሉንም ባለሃብቶች እኩል ነበር የሚመለከታቸው የተሻሻለው ፖሊሲ ግን ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል ሚኒስትሩ አቶ መላኩ፡፡

 

ነገር ግን አሁንም ብዙ ድጋፎች ማድረግ ይጠበቅብናል ያሉት ሚኒስትሩ መንግስት ዘርፉን በተመለከተ በየጊዜው የሚያወጣቸው ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች ለኢትዮጵያውያን አምራቾችን ትኩረት የሰጠ ነው፡፡

 

ከዚህ ቀደም እያመረቱ የነበሩና አሁን ያለውን ቴክኖሎጂ የማይጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ከገብያው እየወጡ ነው ይህ ሚሆነው መወዳደር ስለማይችሉ ነው ብለዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Recent Posts

See All
ኢትዮጵያ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል፡፡

ሐምሌ 22 2018 ኢትዮጵያ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከውሃ የሚመነጨው ድርሻው ከ95 እስከ 96 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ከውሃ በተጨማሪ እንደ ነፋስ ፣ ፀሀይ እንፋሎት ካሉና ሌሎች አማራጮች ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ስብጥሩን የማስፋት ው

 
 
 
የሐምሌ 22 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#አሜሪካ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ውስጥ በአፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ይዞታ ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ሳውዲ ጥቃቱን ከማውገዝ በተጨማሪ መበቀሌ አይቀርም በሚል ዝታ ነበር፡፡ በኢራቆቹ አ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page